Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለዲፕሎማቶች ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች፣ ሚሲዮንና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ማብራሪያ ሰጡ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ሸባሪው ህወሓት እያደረገ ያለውን ትንኮሳና መንግስት እየወሰደ ያለውን የሰላም ጥረት አብራርተዋል።

መንግስት ጦርነቱን በሰላም ለመፍታት ሲዘጋጅ አሸባሪው ህወሓት ግን ለሌላ ዙር ጦርነት ታዳጊዎችን መልምሎ በማሰልጠን ለጦርነት ሲዘጋጅ ነበር ብለዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ያስቀመጠውን የሰላም አማራጭ ወደጎን በመተው ነሐሴ 18 ሦስተኛ ዙር ጦርነት መጀመሩን ገልጸዋል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.