Fana: At a Speed of Life!

የተጀመረው የሰላም ሂደት እንዲቀጥል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመረው የሰላም ሂደት እንዲቀጥል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ፡፡

የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች “የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ በወቅታዊ የሃገሪቱ ሁኔታ እና አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ መግላጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የተጀመረው ጦርነት አብቅቶ የሰላም ውይይት ሂደት እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በተለይም፥ በትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች እና መሪዎች ህወሓት ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመለስ በመምከር እና በመገሰጽ አባታዊ እና መንፈሳዊ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባቸዋል ነው ያሉት።

የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ህወሓት ታዳጊ ህጻናትን ለወታደራዊ ዘመቻ ማሰለፉ ኢሰብአዊ እና የጦር ወንጀል ነው ሲሉ አውግዘዋል።

በመሳፍንት እያዩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.