Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ የኀብረት ሥራ ማኅበራት ለበዓል አስፈላጊ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለዘመን መለወጫ በዓል የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በትጋት እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

እንደሀገር ያለው የምርት አቅርቦትና ግብይት የዜጎችን የመግዛት አቅም ያገናዘበ እንዲሆን የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት እየተከሰቱ ባሉ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ሕዝቡ ለምርት እጥረት ወይም ለዋጋ ንረት እንዳይጋለጥ በትጋት መሥራት እንደሚገባም ነው ኮሚሽኑ ያሳሰበው፡፡

ስለሆነም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የምትገኙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት÷ “ከዚህ በፊት እንደምትደርጉት ሁሉ “ቅድሚያ ለሰው ልጆች” በሚለው መርህ ምርት ከአባሎቻችሁ በመሰብሰብ እና ከሌሎች ሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ጋር በመተሳሰር በወቅቱ፣ በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንድታቀርቡ” ሲል  ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተለይም በመጪው የዘመን መለወጫ የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶችን በማቅረብ በትጋት እንድትሠሩ ሲል ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.