የአፍሪካን የቱሪዝም ሃብት ለማልማት ቻይና ድጋፏን እንድታጠናክር ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የቱሪዝም ሃብታቸውን ለማልማት በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ላይ የቻይና መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ፡፡
በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ በቤጂንግ ከተማ በተካሄደው “በቻይና የዓለም የቱሪዝም ትብብርና የልማት ኮንፈረንስ” ላይ ተሳትፏል።
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኮንፍረንሱ የፓናል ውይይት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፥ የኢትዮጵያን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች እንዲሁም ሀገሪቱ ያላትን የቱሪስት መዳረሻ መስህቦች አስተዋውቀዋል።
እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ ቻይናውያን ቱሪስቶች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድም ወደ አምስት የቻይና ከተሞች እንደሚበርና ቀላልና ቀልጣፋ የቪዛ አሰራር ስርዓት ተግባራዊ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡
አምባሳደር ተሾመ፥ የአፍሪካ ሀገራት የቱሪዝም ሃብታቸውን ለማልማት በሚያደርጉት ሁሉን አቀፍ ጥረት ላይ የቻይና መንግስት መደገፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!