Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በም/ር መስተዳድር የሚመራ ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ ኮሚቴ መቋቋሙን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ ዶክተር ፀጋይ በሪሁ÷ የኮሮና ቫይረስ ከቀን ወደ ቀን ስፋቱ እየጨመረ በመምጣቱ የዓለም ስጋት መሆኑን ነው ያነሱት።

በመሆኑም የክልሉን ህብረተሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል ኮሚቴ በክልል ደረጃ መቋቋሙን ገልፀዋል።

ኮሚቴው የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች አካላትን ያካተተ ሲሆን ÷ ወደ ተግባር መግባቱንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በቫይረሱ የተጠቁ ወይም የተጠረጠሩ ሰዎች ሲገኙ የሚለዩበትና ህክምና የሚያገኙበት ማዕከል በመቐለ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ማዕከሉ 160 አልጋዎችን የያዘ መሆኑን ዶክተር ፀጋይ አብራርተዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.