Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በሀረሪ ከተለያዩ የማህብረሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከምስራቅ፣ ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች፣ ከሀረሪ ክልል እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሀረሪ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዚህ ውይይት ላይ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ፣የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አቶ ለማ መገርሳ ከህብረተሰቡ ለተነሳላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ይህ የሰላም ኮንፈረንስ በሀረሪ ከተማ በሚገኘው ጨለንቆ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው በዛሬው ዕለት የተካሄደው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.