Fana: At a Speed of Life!

አፕል 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ተቀጣ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴክኖሎጂ ኩባንያው አፕል 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ተቀጣ።

ኩባንያው በፈረንሳይ የንግድ ውድድርና ሸማች ባለስልጣን ከንግድ ውድድር ህጉ ውጭ ተንቀሳቅሷል በሚል ነው ለቅጣት የተዳረገው።

ቅጣቱ የተጣለበት መስሪያ ቤቱ በኩባንያው ላይ ለ10 ዓመት ምርመራ ካደረገ በኋላ ነው ተብሏል።

አፕል ከንግድ ውድድር ህጉ ውጭ ዋጋዎችን በመወሰንና በሌሎች የገበያ ተወዳዳሪነት ላይ ተፅዕኖ አሳርፏል በሚል ቅጣቱ እንደተወሰነበትም ታውቋል።

ከዚህ ባለፈም ሁለት የአፕል አከፋፋዮች ላይ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

አካፋፋዮቹ አፕል ገበያውን ብቻውን እንዲቆጣጠር በማሴር ነው ማዕቀብ የተጣለባቸው።

ኩባንያው በፈረንሳይ የ40 ዓመት አገልግሎት በመስጠት ለ240 ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።

 

ምንጭ፦ cnet.com/news/

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.