Fana: At a Speed of Life!

ዋሊያዎቹ ለ2023 የቻን ውድድር አለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የሩዋንዳ አቻውን በማሸነፍ በታሪክ ለሶስተኛ ጊዜ ለቻን አፍሪካ ውድድር አለፈ፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከሩዋንዳ አቻው ጋር አድርጓል፡፡

ቡድኑ በጨዋታው 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለ2023 ቻን ውድድር ማለፉን አረጋግጧል፡፡

የአሸናፊነቱን ጎል ዳዋ ሁቴሳ በቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒየንሺፕ (ቻን) ውድድር በቀጣዩ ዓመት በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.