Fana: At a Speed of Life!

በጭና ንፁሃን የተጨፈጨፉበት 1ኛ ዓመት ታሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ጭና ንፁሃንን በግፍ የጨፈጨፈበት 1ኛ ዓመት ታስቧል፡፡

በመታሰቢያ ዝግጅቱ÷ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ዶክተር ይልቃል በመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የአሸባሪው ህውሓት የወረራ ሙከራ  የተቀለበሰው እና አከርካሪው የተመታው ጭና ላይ መሆኑን አስታውሰው÷በእዚሁ ቦታ ለሀገር መስዋትነት የከፈሉ ዜጎችን ማሰቡ ተገቢ በመሆኑ ቀኑን አክብረናል ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ ያኔ ተሸንፎ ቢመለስም አሁንም ለ3ተኛ ጊዜ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ወረራ መሰንዘሩን ጠቁመው÷ ለዚህም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ሊመክትና እራሱን ከወረራ ሊታደግ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ የወቅቱን ትግል የሚሳይ መዝሙር  ተዘጋጅቶ በርዕሰ መስተዳድሩ  የተመረቀ ሲሆን÷ የተከፈለውን መስዋትነት የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይም  ቀርቧል፡፡

የሽብር ቡድኑ ባለፈው ዓመት በጭና ተክለ ሐይማኖት ቀበሌ በንጹሃን ላይ በፈጸመው ጥቃት÷ ከ100 በላይ ሕጻናት፣ እናቶችና አዛውንቶች በግፍ መጨፍጨፋቸውና የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸው  ይታወሳል፡፡

በኤልያስ አንሙት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.