Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሾችን በከነማ መድሃኒት መደብሮችና ጤና ጣቢያዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል – ኢንጂነር ታከለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስተዳደሩ የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሾችን በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የከነማ መድሃኒት መደብሮችና ጤና ጣቢያዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብ ተናገሩ።

በጎ ፈቃደኞችንና ወጣቶችን በማስተባበር በተለያዩ መንገዶች መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የሚያቀርብና የቅድመ ጥንቃቄ ስራ የሚሰራ ኮሚቴ በከተማ አስተዳደሩ መቋቋሙንም ተናግረዋል።

ችግሩን ለመከላከል ቅድመ ጥንቃቄ ላይ በማተኮር እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ኢንጂነር ታከለ፥ በከተማዋ ውስጥ የተከሰተውን የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሽ እጥረት ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ ሳኒታይዘሮችንና ሌሎች የህክምና መሳሪያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ያቀርባል ብለዋል።

በህዝብ መገልገያ ቦታዎች ላይ የተጀመረውን ግንዛቤ የማስጨበጥና የጥንቃቄ ስራ የከተማ አስተዳደሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በጎ ፈቃደኞችን ያሰባሰበው ኮሚቴም የትራንስፖርትና ህዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ግንዛቤ በመስጠት እንዲሁም የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለሚፈልጉ ድጋፉን እንዲያገኙ የማስተባበር ስራን ያከናውናል ነው ያሉት።

ህብረተሰቡም ሳይደናገጥ የግል ንጽህናውን እንዲጠብቅና ጥርጣሬ ሲኖረው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.