Fana: At a Speed of Life!

በመጪው አዲስ ዓመት ሁሉም ዜጋ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት መስራት አለበት-ዶ/ር ቀንዓ ያደታ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው አዲስ ዓመት ከምንጊዜውም በላይ ሁሉም ዜጋ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ቀንዓ ያደታ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ጋር በ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣ በ2015 ዓ.ም እቅድ እና በወቅታዊ ሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ ላይ እየተወያየ ነው፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የውይይት መድረክ የተገኙት ዶክተር ቀንዓ ያደታ እንዳሉት÷ በመጪው አዲስ ዓመት የመዲናዋ ነዋሪዎች ከምንጊዜውም በላይ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከጸጥታ ኃይሉ በተጨማሪ ህዝባዊ አደረጃጀቶችን ወደ ስራ በማስገባት በሁሉም ረገድ ለውጦች መታየታቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡

በመድረኩ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለ3ኛ ጊዜ ሀገር ለማፈራረስ የጀመረውን ወረራ በአንድነት መመከት እንደሚገባ መገለጹን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው የጸጥታ ችግር የሚፈጥሩ አካላትን ሲመለከቱም ለሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት እንዲጠቁሙ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.