Fana: At a Speed of Life!

ጳጉሜን በመደመር” በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃድ ቀን በመዲናዋ መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን በመደመር” በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃድ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ መከበር ጀመረ።

በእለቱ በማለዳ በሁሉም ክፍለከተሞች አካባቢን ማጽዳት፤ ችግኝ ተከላና የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎችን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃለፊዎችም ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ተገኝተው የበጎ ፍቃድ ቀንን አካባቢን በማጽዳት አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ዛሬ አመቱን ሙሉ በበጎነት ስናከናውን የቆየነውን ተግባር የምናጠናቅቅበት ዕለት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዕለቱ ከሁሉም በላይ አሸባሪውን ህወሃት በከፈተብን ጦርነት ለኛ መኖር፤ ለኛ ሰላም እና ለሉአላዊነት ሕይወትቱ በመስጠት መስዕት እየከፈለ ያለውን ለመከላከያ ሰራዊታችን እንዲሁም ጥምር ጦሩ እየሰጡ ያለውን ጎነት የለምና ምስጋና ይገባቸዋል ማለታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.