Fana: At a Speed of Life!

ከአሸባሪው ህወሓት ምሽጎች የእርዳታ ድርጅቶች በተረጂዎች ስም ያስገቧቸው ቁሳቁስ ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው የህወሓት አመራሮች ያዋጉባቸው በነበሩ ምሽጎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በተረጂዎች ስም ያስገቧቸው የመጠለያ ቁሳቁስ መገኘታቸውን የመከላከያ ሰራዊት አስታውቋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን የማፈራረስ ህልሙን ለማሳካት ጥቃት በከፈተበት የወልቃይት ግንባር ነው የሽብር ቡድኑ አመራሮች ያዋጉባቸው በነበሩ ምሽጎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በተረጂዎች ስም ያስገቧቸው የመጠለያ ቁሳቁስ የተገኙት፡፡

አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ ድርጅቶች ለተቸገሩ ወገኖች የሚለግሡትን ምግቦች  ከዚህ ቀደም ለውጊያ በተደጋጋሚ እየተጠቀመበት እንደነበር መገለጹ አይዘነጋም።

ቡድኑ ከሠሞኑ በከፈተው ጦርነት በምግብ እጥረት ለተጎዱ ዜጎች የሚቀርበውን ኮርን ሶያ ብሌንድ የተሰኘ አጣዳፊ የምግብ እጥረትን ለማከም የሚውል የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያን አሟልቶ የተዘጋጀውን አልሚ ምግብ ለታጣቂዎቹ እንደተጠቀመ ተረጋግጧል።

ይህ አልሚ ምግብ ዜጎችን ከርሀብና ሞት የሚታደግ እና የሚያክም መሆኑን ይነገራል።

አሸባሪው ቡድን ዜጎች በርሃብ ተሰቃይተው ለህልፈት እየተዳረጉ እሱ ግን በምሽግ ከዝኖ ታጣቂዎችን እየቀለበ እንደሚያዋጋበት ማረጋገጥ መቻሉን ነው የመከላከያ ሰራዊት መረጃ የሚያመላክተው።

ቡድኑ ከዚህ ባለፈም በህዝብ ስም ወደ ትግራይ የሚገባውን እህል ከተቸገረው ህዝብ ቀምቶ ለታጣቂዎቹ ብቻ እንደሚያቀርብ በሰሞኑ በሰራዊቱ ላይ በከፈተው ጦርነት ምሽጉ ሲሰበር ተጋልጧል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.