Fana: At a Speed of Life!

በጎነት እና ስራ ፈጣሪነት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አምላክቸር ስዩም ለበርካታ ሰዎች በነፃ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች አሰራር ስልጠና በመስጠት ራሳቸውን እንዲችሉ ምክንያት የሆኑ ሰው ናቸው፡፡

በቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሳልማ ፈርኒቸር ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አምላክቸር ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ በሀገሪቱ በርካታ ስራ አጥ ወጣቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ያለው የኢንዱስትሪ ዘርፍ በርካታ የሰው ሀይል የሚፈልግ ቢሆንም የሚፈለገውን ያህል ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ማግኘት ግን አስቸጋሪ መሆኑን ይናገራሉ።

በመሆኑም ባቋቋሙት የቤትና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች መስሪያ ድርጅት ስራ አጥ ወጣቶችን በነፃ ስልጠና በመስጠት እና የስራ ክህሎት ካዳበሩ በኋላም በድርጅታቸው ተቀጥረው እንዲሰሩ እንድሚያደርጉም ነው የተናገሩት።

ሰዎች የሙያ ስልጠና ወሰደው ወደ ስራ የሚገቡ ከሆነም የኢንዱስትሪ ዘርፉን ጨመሮ ራሳቸውን፣ ሀገራቸውን እና ቤተሰባቸውን መጥቀም የሚችሉ ዜጎች ሊሆኑ እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

በዚህ ዘርፍ ስራዎች በስልጠና መልክ እንዲስፋፉ አይደረግም የሚሉት አቶ አምላክቸር ይህ ባህል ተቀይሮ የሙያ ስልጠናዎች በሁሉም ቦታ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ እሰራለሁ ብለዋል፡፡

በሳልማ ፈርኒቸር ውስጥ ስልጠና ወስደው እና እዛው ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች በበኩላቸው በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ህይወታቸውን ያሳልፉ እንደነበር ገልፀው በተሰጣቸው ስልጠና ግን የሙያ ባለቤት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሚሰሩት ስራ እና በሚያገኙት ገቢም ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን እያስተዳደሩ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.