Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሠራዊት ለመስጠት ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

አመራሮቹ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላ እንዳሉት÷ አሸባሪው ህወሓት የተሰጠውን ተደጋጋሚ የሰላም አማራጭ በመግፋት ለሶስተኛ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ ጦርነት ከፍቷል።

በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከትም የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት የሚጠበቀው መላው ህዝብ በሚያደርገው አስተዋጽኦ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ ከፍተኛ አመራር የአንድ ወር ደመወዙን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመለገስ ቃል መግባቱን ገልፀዋል።

አመራሮቹ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከመለገስ በተጨማሪም በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.