Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በበጎ ፈቃድ አርዓያ ተግባር ለፈጸሙ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅናና ምስጋና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተከበረው “የበጎ ፍቃድ ቀን” በአዲስ አበባ ከተማ በተለየዩ መስኮች በበጎ ፈቃደኝነት አርዓያ ተግባር የፈጸሙ ተቋማትና ግለሰቦች ከከተማ አስተዳደሩ እውቅናና ምስጋና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በእውቅናና ምስጋና መርሐ ግብሩ በጎ ፍቃደኞችን ያመሰገኑት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ ለሕዝቦች ሰላም ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን እየሰጡ ላሉት የመከላከያ ሠራዊቱና ጥምር ኃይሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በዓመቱ በበጎ ተግባራት በርከታ ስራ ተከናውኗል ያሉት ከንቲባዋ፥ ይህንን እንደ ልምድ ወስደን በቀጠይ የተሻለ ሥራ እንድናከናውን ሁለችንም ብርቱ ሆነን የበጎ ፍቃድ ሥራ ለመተግበር እንነሳ ብለዋል።

ይህን የበጎ ተግባር ዝቅ ብለው በመወረድ አርዓያ ሆነው ላስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምስጋናና እውቅና የተሰጣቸው ግለሰቦችና ተቋማት ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት በምገባ ማእከላት፣ የዳቦ ማምረቻና መሸጫ ሱቆች፣ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታና እድሳት እና ሌሎች የልማት ስራዎች ላይ የተሳተፉ ናቸው ተብሏል።

በዚህም በጎ ፈቃደኞቹ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን ተሰልፈው ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጎ ስራዎችን አከናውነዋል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.