Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት አንድ እናትና አራት ልጆቿን ጨምሮ 25 ንጹሃንን ረሸነ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን አባላት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ወለህ የመጠለያ ጣቢያ ገብተው 25 ንጹሀንን በግፍ ረሽነዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያው አንዲት እናት ከአራት ልጆቿ ጋር በግፍ መረሸኗም ታውቋል።

ከጥቃቱ የተረፉ የዐይን እማኞች እንደገለጹት÷ አሸባሪ ቡድኑ በመጠለያ ጣቢያው ያላደረሰው ግፍ የለም፤ ፍጹም እንዳንነሳ አድርጎን ነው የሄደው ብለዋል፡፡

በግፍ ከተገደሉ 25 ንጹሀን መካል አብዛኞች ሕጻናትና ሴቶች ሲሆኑ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ጭምር በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የዋግኽምራ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው አረመኔው ህወሓት ከዚህ ቀደም ከ90 ሺህ በላይ ወገኖች ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል፡፡

ዛሬም ይህን እኩይ ተግባር አዝሎ የመጣው ትህነግ በመጠለያ ጣቢያ ገብቶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

በእርዳታ የተሰጣቸውን የዕለት ጉርስ ጭምር የዘረፈው የሽብር ቡድኑ÷ የመጠለያ ጣቢያውን ቁሳቁስ ጭምር ማውደሙንም ነው ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች የተናገሩት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.