Fana: At a Speed of Life!

በአየር ጠባይ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የሀገር ውስጥ በረራዎች ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ከትናንት በስቲያ በአየር ጠባይ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የሀገር ውስጥ በረራዎች መጀመራቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።

አየር መንገዱ በረራዎቹ በመቋረጣቸው መንገደኞች መጉላላት አጋጥሟቸዋል ሲል ገልጿል።

ሆኖም በአሁኑ ወቅት በረራዎቹን ያስተጓጎለው የአየር ንብረት በመስተካከሉ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን በመመደብ መጉላላት ያጋጠማቸውን ደንበኞቹን ለማስተናገድ እንደሚሰራ አየር መንገዱ ተናግሯል ።

በዚህም ከትናንት ጀምሮ በረራዎቹን እንደቀጠለ አስታውቋል።

ወደ ደሴ የሚደረገው በረራ በአካባቢው በተከሰተው የአየር ጠባይ ለውጥ እንደተስካከለ የበረራውን መጀመር አየር መንገዱ በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትናንት በስቲያ ወደ መቐለ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሁመራ፣ አክሱም፣ ሽሬና ላልይበላ ሊያደርግ የነበረውን በረራዎች በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት መሰረዙ ይታወሳል።

ምንጭ÷ኢዜአ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.