Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምራች ቀንን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ወቅት ከንቲባ አዳነች፥ እስካሁን ባለው በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ተቋቁማችሁ እየሰራችሁ ትገኛላችሁ ብለዋል።

አያይዘውም እኛም ለጥረታችሁ ዕውቅና እየሰጠን የጎደለውን ከመሙላት መቼም ወደኋላ አንልም ነው ያሉት።

አክለውም መሬትን፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትን፣ የፋይናንስ አቅርቦትንና ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር የሚደረግ ቅንጅታዊ አሰራርን ጨምሮ ከተማ አስተዳደሩ የዘርፉን አጠቃላይ ማነቆዎች እየለየ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ፥ አስተዳደሩ አምራቹን በሚፈለገው ደረጃ እንደሚያዳምጥ ነው የተናገሩት።

በከተማዋ የሚገኙ ከ10 ሺህ በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ግዙፍ ኩባንያ መሸጋገር እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.