Fana: At a Speed of Life!

ከነበሩብን ጫናዎች አንጻር የ2014ዓ.ም አፈጻጸም ስኬታማ ነበር- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገራችን ላይ ከነበሩ ዘርፈ ብዙ ጫናዎች አንጻር የ2014ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ስኬታማ ነበር ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የ2014ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2015 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በሀገራችን የሰሜኑ ግጭት ጋር በተያያዘ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን የነበሩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች እና የሚዲያ ዘመቻ እንዲሁም ከኮቪድ ጫናዎች አንጻር ሚኒስቴሩ የተሻለ አፈጻጸም አሳይቷል፡፡

በዲፕሎማሲው በኩል በአገራችን ላይ የተደቀኑ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ እና ወዳጆችን ለማበራከት ከፍተኛ ሥራ መሠራቱንም ገልጸዋል፡፡

በአገራችን ለይ አሉታዊ አቋም የያዙ አካላትን ለማለዘብና ለማስገንዘብ የተዘጋጀው ዕቅድ ውጤት አምጥቷል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የሪፎርሙ ሥራ የአደረጃጀት ለውጦችን እና ተገቢ የሰው ኃይል በማሰማራት የተከናወነው ሥራ አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.