Fana: At a Speed of Life!

ፋና ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የሥምምነት ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚስችለውን የሥምምነት ሰነድ ተፈራረመ።

ስምምነቱንም፥ አቶ አድማሱ ዳምጠው የፋና ብሮድካስትንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ባይሳ ለታ ተፈራርመዋል።

የጋራ ሥምምነት ሰነዱ በዋናነት ከመማር ማስተማሩ ስራ ባሻገር፥ በዩኒቨርሲቲው የሚከናወኑ ማህበረሰብ ተኮር ጉዳዮችን በሚዲያ ተደራሽ ማድረግ ላይ የሚያተኩር ነዉ።

ፋና ብሮድካስትንግ ኮርፖሬት ወቅታዊ፣ አዝናኝና አስተማሪ መረጃዎችን ባሉት የሚዲያ አውታሮች በኩል በፍጥነትና በጥራት የሚያደርስ በመሆኑ ለዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲዉ በተማሪዎች አገልግሎት፣ በትምህርት ልህቀት፣ በማህበረሰብ ዓቀፍ የልማት ስራዎችና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን የሚያስተዋውቅበትም እንደሚሆን ተመልክቷል።

አምቦ ዩኒቨርሲት አራት ካምፓሶች እና አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ያለው ሲሆን፥ በ67 የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ባይሳ ለታ፥ ዩኒቨርሲቲው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንና በቀጣይም ህብረተሰብ ተኮር ስራዎችን በጋራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ ከፋና ጋር የዩንቨርሲቲውን ገፅታ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራ ያከናውናል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ከፋና ጋር ትውልድን ለማነፅ የሚያግዙ ሰው ተኮር ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ደግሞ፥ የፋና ብሮድካስትንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ናቸው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ የዛሬው ስምምነት ተቋሙ ለሚሰራቸዉ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎች ትኩረት የሰጠ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የሚዲያ ተቋሙ በርካታ ስራዎችን ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ከዩንቨርሲቲው ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ ወቅት አረጋግጠዋል።

በዘቢብ ተክላይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.