Fana: At a Speed of Life!

በፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆኑ ሰራተኞች ከመስከረም 1 ቀን ጀምሮ በጡረታ ዐቅድ ይካተታሉ ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆኑ ሰራተኞችን ወደ ጡረታ ዐቅድ የማካተት አሰራር ከመስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የግል ድርጅቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አስታወቀ።
የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገመቹ ዋዩማ በሰጡት መግለጫ ከመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ የአዋጅ ማሻሻያ በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል።
በዚህም በፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የነበሩ ሰራተኞችን በግል ድርጅት ሰራተኞች የጡረታ ዐቅድ ስለሚሸፈኑበት ሁኔታ መመሪያ ማውጣት ከአዋጁ ማሻሻያ ውስጥ አንዱና መሰረታዊ መሆኑን አስረድተዋል።
መመሪያው በግል ድርጅት ሠራተኞች ዐቅድ ያልተሸፈኑ ሰራተኞች በጡረታ ዐቅድ የሚሸፈኑበት እና የተጠራቀመ የፕሮቪደንት ፈንድ ገንዘብ ለጡረታ ፈንድ ገቢ በማድረግ ቀደም ሲል የፈጸሙት አገልግሎት ለጡረታ አበል አወሳሰን እንዲታሰብ ያስችላል ብለዋል።
አያይዘውም መመሪያው ከ2003 ዓ.ም በፊት በተቋቋሙና የግል ድርጅት ከነበራቸው ፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚነታቸውን ለመቀጠል ወስነው የቀጠሉ እንዲሁም በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድ ያልተሸፈኑ የግል ድርጅት ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናልም ነው ያሉት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.