Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ደሚቱ መንግስት ሰላምን ለማስፈን እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት ለስሎቬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብራሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሰላም አማራጮችን አሻፈረኝ ብሎ የጥፋት እጆቹን ለጦርነት በመዘርጋት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥፋት ማድረሱን በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ደሚቱ ከስሎቬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታንጃ ፋጆን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም፥ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን፥ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዘርፎች ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መግባባት ላይ ደርሰዋል።

አምባሳደሯ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም መንግስት ሰላምን ለማስፈን እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስረድተዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ሕፃናትን ለጦርነት እየመለመለ እንደሆነ አምባሳደር ደሚቱ አስረድተዋል፡፡

ለእርዳታ ወደ ክልሉ የገቡ ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶችን፣ በቅርቡም የዓለም የምግብ ፕሮግራም መጋዝንን እንደዘረፈም ለሚኒስትሯ አስረድተዋል።

የስሎቬኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታንጃ ፋጆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ታሪካዊ ግንኙነት እንዳለ ገልፀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርሯ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በጋራ መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡

በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነትን ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ሮም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.