Fana: At a Speed of Life!

የአገልጋይት ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላ ሀገሪቱ የአገልጋይት ቀን በጎ ተግባራትን በመከወን እየተከበረ ነው፡፡

የአገልጋይነትን ቀን በማስመልከት የሥራና ክህሎት፣ የቱሪዝም እና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች “አገልጋይነት ከእኔ ይጀምራል” በሚል መሪ ሐሳብ በእንጦጦ የፅዳት አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡

ከጽዳት አገልግሎቱ በተጨማሪ ዕለቱን የተለያዩ በጎ ተግባራትን በማከናወን እንደሚያከብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፥ ተገልጋዮች አገልጋዮችን የሚያመሰግኑበት ይህ ቀን የአገልጋይነት ባህልን ለማዳበር እና ተገልጋዮችም ማመስገንን እንዲለማመዱ የሚያስችል ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.