Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለዩክሬን እና ጎረቤት ሀገራት የ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ጦር መሳሪያ ድጋፍ ቃል ገባች

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን እና ጎረቤት ሀገራት ተጨማሪ የ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በዩክሬ ዋና ከተማ ኪዬቭ ድንገተኛ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በኪዬቭ ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ዜለንስኪ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም የአሜሪካ መንግስት ለዩክሬን እና 18 ጎረቤት ሀገራት በሚያደርገው የ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ጦር መሳሪያ ድጋፍ ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

የጦር መሳሪያ ድጋፉ ሩሲያ በቀጣይ በዩክሬን እና ጎረቤት ሀገራት ብሎም በቀጣናው ልትፈጥር የምትችለውን ስጋት ለመቋቋም ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከሚደረገው የ2 ነጥብ 2 በሊየን ዶላር ጦር መሳሪያ ድጋፍ ውስጥም 1 በሊየን ዶላር የሚያወጣው ለዩክሬን መንግስት የሚሰጥ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ቀሪው ድጋፍ አልባኒያ፣ ቦስኒያ፣ ቡልጋሪያ እና ክሮሺያን ጨምሮ ለዩክሬን ጎረቤት ለሆኑ 18 ሀገራት የሚሰጥ እንደሆነ መገለጹን አር ቲ ዘግቧል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ዜለንስኪ አንቶኒ ብሊንከን ላደረጉት ጉብኝት እና ዋሺንግተን ለምታደርገው የጦር መሳሪ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.