Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው÷እንደ ሀገር ባለፉት አራት ዓመታት በርካታ እንቅፋቶችና መሰናክሎች ያጋጠሙ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ በጋራ እና በአንድነት በመቆም አገር እንድትበተን የተሸረቡ ሴራዎችን በማክሸፍ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ እንገኛለን ነው ያሉት አቶ ሙስጠፌ።
 
በአዲሱ ዓመትም የገጠሙንን የውስጥና የውጭ ጠላቶቻች እኩይ ሴራ በመሻገር ለኢትዮጵያ ሰላም የሚመጣበት፣ ለህዝቦቿም የመረጋጋት ዘመን እንዲሆን መመኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም እንኳን ለአዲሱ የ2015 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.