Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ791 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ 791 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ።

የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት 802 ታራሚዎች መካከል 791ቱ የይቅርታ መስፈርት አሟልተው የተፈቱ ሲሆን÷ 11ዱ ደግሞ የተፈረደባቸው የእስራት ዓመት የተቀነሰላቸው ናቸው፡፡

ታራሚዎቹ በይቅርታ የተፈቱት በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ያገኙትን የማረምና ማነፅ ትምህርት ተግባራዊ ያደርጋሉ ተብሎ የታመነባቸው መሆናቸውን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ተናግረዋል።

የይቅርታ ተጠቃሚ የሆኑት በይቅርታ አዋጅ መሰረት በቦርዱ የተረጋገጠ እና ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቀርቦ የጸደቀላቸው ናቸው፡፡

በይቅርታ የተፈቱት ታራሚዎች በሕክምና ቦርድ የተረጋገጠ ከባድ ታማሚ የሆኑ፣ ሕጻናት የያዙ እናቶች፣ ከ60 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ አረጋውያን መሆናቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይቅርታው የሞት ፍርደኞችን፣ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል የፈጸሙና በከባድ የግድያ ወንጀል የተፈረደባቸውን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ታራሚዎችን እንዳላካተተ አቶ ተክሌ ገልጸዋል።

ሃላፊው ለመላው የኢትዮጵያ እና የክልሉ ህዝብ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.