Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፌደራልና ክልልና የጤና ቢሮ ሀላፊዎች እንዲሁም የኮሙዩኒኬሽን አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌደራልና ከክልል ኮሙዩኒኬሽን አመራሮች እንዲሁም ከክልል ጤና ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ ከኮሙዪኬሽን ቢሮ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በኮሮናቫይረስ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

በመድረኩም በኮሮናቫይረስ (በኮቪድ -19) ግንዛቤ ላይ እና ዕውቀትን የማሳደግ ጥረቶች ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

በየደረጃው ለሚገኘው ሕዝብ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በማስተላለፍ የማረጋጋት ሚናን ከመጫወት አንፃር የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ወሳኝ ድርሻ አላቸው ብለዋል።

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ማስረጃን መሰረት ያደረገ መረጃን በማሰራጨት ለመከላከል እና ስርጭቱን ለመግታት የማይተካ ሚና እንዳላቸውም አስታውቀዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የፌደራል እና የክልል ኮሙዪኬሽን አመራሮች እንዲሁም የክልል የጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.