Fana: At a Speed of Life!

በ2014 የውስጥ ባንዳዎች ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር  ቢፈትኑንም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እኩይ አላማቸው ሳይሳካ ቀርቷል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው ዓመት የውስጥ ባንዳዎች ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመተባበር ቢፈትኑንም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እኩይ አላማቸው ሳይሳካ ቀርቷል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ የ2015 አዲስ ዓመትን አስመልክተው ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም፥ ባለፈው ዓመት ሀገር እና ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል፡፡

በአንፃሩ  የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከውስጥ ባንዳዎችና ተላላኪዎች በመተባበር በሀገር ሉዓላዊነት ላይ አደጋን ደቅነው እንደነበር  ነው ያነሱት ፡፡

ይሁን እንጅ መላው ኢትዮጵያውያን የሀገር ነፃነት እና ከብርን ለማስጠበቅ ባደረጉት ተጋድሎ የጠላቶች እኩይ አላማ ሳይሳካ መቅረቱን አስገንዝበዋል፡፡

ለዚህም መላው ኢትዮጵያውያን እና የጸጥታ ሃይሉ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ላሳዩት ተጋድሎ እና ለከፈሉት መስዋዕትነት ምክትል ፕሬዚዳንቱ በራሳቸው እና በፓርቲው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠላቶቻችን በቀጣይም እኛን መፈተናቸው አይቀርም ያሉት አቶ አደም ፋራህ፥  ፈተናውን ማለፍ የምንችለው የሃሳብ ልዩነቶችን እና የውስጥ ጉዳዮችን በዴሞክራሲያዊ አካሂድ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ሲቻል ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም የብልፅግና ፓርቲ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን  ነው ያረጋገጡት ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ በ2015 ዓመተ ምህረት የፓርቲውን ተቋማዊ አቅም በመገንባትና የውሰጠ ፓርቲ አንድነት እና ዲስፕሊን በማጠናከር መንግስት የመምራት ሚናውን እንደሚወጣም ጠቁመዋል፡፡

ዜጎች የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማፋጠን በሚደረርገው ጥረት እንደ ከዚህ ቀደሙ  ከፓርቲው ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.