Fana: At a Speed of Life!

ሳፋሪኮም የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ በአዳማ እና ባሕር ዳር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተከታታይ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ በአዳማ እና ባሕር ዳር ከተሞች መጀመሩን አስታወቀ፡፡
 
የአዳማ እና ባሕር ዳር ደንበኞች በ07 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
 
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርድ ደንበኞች ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል የያዘ ነው ተብሏል፡፡
 
በተጨማሪም ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
 
በሙከራ ኔትወርኩ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎች ማድረግ እንደሚችሉም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.