Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባ በያዝነው መስከረም ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአልጄሪያ በነበራቸው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከሀገሪቷ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት የቀጣይ ዙር የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባም በቅርብ ጊዜ እንዲካሄድ ሥምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።

በዚሁ መሰረት የኮሚሽኑ ስብሰባ በያዝነው ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ገልጸዋል።

በስብስባው ኢትዮጵያና አልጄሪያ በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ቀጥታ የአየር በረራ እንዲኖር በማድረግ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በጋራ ኮሚሽኑ ስብስባ በኢትዮጵያና በአልጄሪያ መካከል በተለያዩ መስኮች የተፈረሙ ስምምነቶች ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግም አምባሳደሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሁለቱ ሀገራት የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ለአራት ዙሮች ምክክር ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.