Fana: At a Speed of Life!

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 አዲስ ዘመን መለወጫ በዓል በመላው ኢትዮጵያ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በጥበቃ ላይ የተሰማሩት የጸጥታና የደህንነት አካላት ከራሳቸው በፊት ህዝቡን በማስቀደም የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የታለመውን ግብ ማሳካታቸው ተጠቁሟል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚጠበቀባቸውን ሃላፊነት ለተወጡ አካላትም የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ምስጋና አቅርቧል።

በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ ላበረከተው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ምስጋና ማቅረቡን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይ የሚከበሩ ሃይማኖታዊ፣ ህዝባዊ እና መንግስታዊ ሁነቶች ያለምንም የፀጥታ ስጋትና ችግር በድምቀት እንዲከበሩም ሕብረተሰቡ ቀና ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.