Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሠራዊትና በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ይቀጥላል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግንባር ለተሰለፉ የመከላከያ ሠራዊትና በክልሉ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ።

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንደገለጹት÷ የአሸባሪው ህወሓት ሀገር የማፍረስ ሴራ እንዳይሳካ ሕይወት እየከፈለ የሚገኘውን ሠራዊት በስንቅ፣ በሞራልና በሰው ኃይል መደገፍ ይገባል፡፡

ለመከላከያ ሠራዊት ተገቢውን ድጋፍና ክብር መስጠት እንደሚገባ በማንሳትም÷ የክልሉ መንግሥት ለሠራዊቱ እያደረገ የሚገኘውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ለዚህም የክልሉ አመራሮች ለመከላከያ ሠራዊትና በክልሉ በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የደመወዛቸውን 30 በመቶ ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል ነው ያሉት።

በቀጣይም የንግዱን ማህበረሰብ፣ በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶችና ሌሎች አካላትን በማስተባበር ድጋፍ ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ጠቁሟል፡፡

ሰሞኑን የክልሉ መንግስት በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.