Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2015 በጀት ዓመት 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

የኦሮሚያ ክልል የ2015 በጀት ዓመት የመስኖ ስንዴ ልማት ንቅናቄ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በተያዘው በጀት ዓመት 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክረምቱ እርሻ 1ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ ለማልማት ታቅዶ 1 ነጥብ 63 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በገመቹ ቤኩማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.