Fana: At a Speed of Life!

ለወቅታዊ ጉዳዮች የሚውል ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ እና የገንዘብ ሚኒስቴሮች ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለወቅታዊ ጉዳዮች የሚውል ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ አስጀምረዋል።

ለአንድ ወር የሚቆየው ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄው በትናንትናው እለት በበይነ መረብ በይፋ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በሁሉም ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች  የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው በጀት አመት በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ የተመዘገቡ ስኬቶች እና ክፍተቶች የተዳሰሱ ሲሆን በተለይ ለሀገራዊ ጉዳዮች ቴክኖሎጂን የመጠቀም ልምድ እንደ ጥንካሬ ተነስቷል።

አምባሳደር ብርቱካን በሁሉም ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ሚሲዮኖች ቴክኖሎጂን በመጠቀም የገቢ ማሰባሰብ ስራው እንዲቀላጠፍ የበከሉላቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በማስጀምሪያ መርሐ ግብሩ ከሚኒስትሮቹ በተጨማሪ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.