Fana: At a Speed of Life!

ባህር ዳር ከተማ ደግአረገ ይግዛውን በአሰልጣኝነት ሾመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደግአረገ ይግዛው የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ፡፡

የቀድሞው የክለብ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም አሠልጣኙ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖራቸውም ከቡድኑ ጋር እንደማይቀጥሉ መገለፁ ይታወቃል።

ክለቡ በእርሳቸው ምትክም አሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በአሰልጣኝነት ሾሟል።

የቀድሞ የአውስኮድ እና ኢኮስኮ አሠልጣኝ ደግአረገ 2012 እና 2013 የውድድር ዓመትን በወልቂጤ ከተማ ያሳለፉ ሲሆን ፥ ዓምና ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሠልጣኝነት ህይወታቸውን መቀጠላቸው አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ በሊጉ ዳግም ለማሰልጠን የሦስት ዓመት ውል ፈርመው ባህር ዳር ከተማን መቀላቀላቸውን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እንዲሁም እስካሁን በይፋ ሳይሾሙ በሥራ ላይ የነበሩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በሁለት ዓመት ውል ኢትዮጵያ መድንን ተረክበዋል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከስምንት ዓመታት በኋላ ዳግም በመመለስ ተሳታፊ መሆኑን ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡

አሰልጣኙም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀርበው ለሁለት ዓመት ክለቡን ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸውን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ ይግዛው ብዙዓየሁ አሳውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.