Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ እና ተመድ ተቀራርበው ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ተመድ የዓለም አቀፉን የምግብ ደኅንነት ለማረጋገጥ ትብብራቸውን ለማጠናከርና ተቀራርበው ለመሥራት መስማማታቸው ተገለጸ፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን እና የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዩክሬን እና በተለያዩ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የዓለም የምግብ ደኅንነት፣ የምግብ እህል አቅርቦት ስምምነት እንዲሁም በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ስለዘለቀው ግጭት ከመከሩባቸው ርዕሰ-ጉዳዮች መካከል ዋናዎቹ መሆናቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ÷ ድርጅቱ በሩሲያ የግብርና ውጤቶች እና የአፈር ማዳበሪያ ላይ የጣለውን የወጪንግድ ማዕቀብ ለማንሳት እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን በሥልክ በተካሄደው ውይይታቸው ገልጸውላቸዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በአውሮፓ ትልቁ የኃይል ምንጭ ማብላያ በሆነው እና ዩክሬን ውስጥ በሚገኘው የዛፖሪዢያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጉዳይ ላይ መምከራቸውም ነው የተነገረው፡፡

የኒውክሌር ኃይል ማብላያ ጣቢያው በዩክሬን ቢገኝም ከፈረንጆቹ መጋቢት ወር ጀምሮ ሩሲያ ስታስተዳድረው ቆይታለች፡፡

ሩሲያ በኒውክሌር ኃይል ማብላያው አቅራቢያ ዩክሬን ጥቃት ፈጽማለች ማለቷን ተከትሎ ጉዳዩ እንዳሳሰባት እና የ“ቼርኖቤሉ” ዓይነት አደጋ እንዳይደገም ሥጋት እንዳላት ስትገልጽ መቆየቷ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.