Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የአባይ ድልድይ ግንባታ አፈፃፀም 76 በመቶደርሷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት አፈጻጸም 76 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ፡፡

የድልድዩን ዋና ዋና ስራዎች በእቅዱ መሰረት ለማከናወን አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ድልድዩ ሲጠናቀቅ በሁለቱም መስመር ከሚኖረው 760 ሜትር “ግራይደር” ርዝማኔ ውስጥ 511 ሜትሩ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የድልድዩ ተሸካሚ ምሰሶዎች እና ከመሬት በታች የድልድዩ የቋሚ ተሸካሚ መሰረቶች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን ነው አስተዳደሩ የገለጸው ፡፡

በተጨማሪም፥ ለድልድዩ የሚያስፈልጉ 8 ቋሚ ተሸካሚ መሰሶዎች ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቃቸው እና የተቀሩት በቅርቡ ለመጨረስ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቀጣይ 3 ወራት ውስጥ የድልድዩን ዋነኛ አካል “ግራይደር” ሙሉ ለሙሉ ለመግጠም በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል።

የድልድዩ ግንባታ እየተከናወነ የሚገኘው በመንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀት በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ ተቋራጭነት ነው።

አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ በባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው እየተገነባ የሚገኘው።

ይህ ዘመናዊ ድልድይ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ጎን ለጎን ምቹ የሆነ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እንደሚያስችል ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.