የአራዳና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተሞች ለሰራዊቱ የአይነት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች ለመከላከያ ሰራዊት ከ42 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ 133 በሬዎች፣ 133 በጎች እና 67 ፍየሎች እንዲሁም ደረቅ ስንቅ፣ አልባሳት፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ እና አንሶላ ያካተተ መሆኑን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የአራዳ ክፍለ ከተማ ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ21 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ያሰባሰበውን ድጋፍ አስረክቧል፡፡
ድጋፉ 50 ሰንጋ በሬ ፣ 186 በግ፣ 22 ፍየልና ደረቅ ምግቦች እንዲሁም ከ16 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!