Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ትግበራ ችግር ፈቺ የሆነ ትውልድን ለመፍጠር ሚናው ከፍ ያለ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ትግበራ ሀገር በቀል እውቀትን በመጠቀም ችግር ፈቺ የሆነ ትውልድን ለመፍጠር ሚናው ከፍ ያለ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር አዲሱን ስርዓተ ትምህርት የሙከራ ጊዜ ትግበራ እና የሙሉ ጊዜ ትግበራን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫው በሚኒስቴሩ የስርዓት ትምህርት ማበልጸጊያ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ዛፉ አብርሃም÷ የሙሉ ጊዜ ትግበራ ከ1 እስከ 8ኛ ክፍል የሙከራ ትግበራ ደግሞ ከ9 እስከ 10ኛ ክፍል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሙከራው ትግበራ በሚኒስቴሩ ድረ ገጽ፣ በመምህራን እና በተማሪዎች እጅ ከደረሰ በኋላ ማህበረሰቡ በሚሰጠው የማሻሻያ ጥቁማ ዳብሮ በ2016 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆንም አስታውቀዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.