Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በከፊል ሊዘጉ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በከፊል እንደሚዘጉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በሰጡት መግለጫ ፍርድቤቶች ከመጋቢት 10 እስከ መጋቢት 24 የሚዘጉ ሲሆን በዚህም ጊዜ አዳዲስ መዝገቦች አይከፈቱም ብለዋል።

የጊዜ ቀጠሮ ፣ የዋስትና ሌሎች መሰል አስቸኳይ ጉዳዮች ጨምሮ ከሀገር ፀጥታና ደህንነት ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች እየተመዘኑ በተረኛ ችሎት ይታያሉ ነው ያሉት፡፡

በእነዚህ ጊዜያት ተቀጥረው የነበሩ መዛግብት ከመጋቢት 24 በኋላ እንደ ጉዳዮቹ አይነት ዳኞች ከረዳት ዳኞች ጋር በመሆን ያሸጋሽጋሉ ተብሏል።

በዚህም ዝግ የሚሆኑ ችሎቶች፣ በዳኞች ለቀጣይ የሚሰጡ የመዝገብ ዝርዝርና ቀጠሮዎች በፍርድ ቤት እንዲለጠፋ ይደረጋል ነው የተባለው።

ፍርድ ቤቶች በሚዘጉበት ጊዜ ዳኞች ለመዝገቦች ውሳኔ ለመስጠት ቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩም ፕሬዚዳንቷ ተናግረዋል።

በታሪክ አዱኛ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.