Fana: At a Speed of Life!

ኳታር ለኩላሊት ህክምና ማዕከል የ18 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ተፈራረመች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኳታር በአዲስ አበባ ለሚገነባው የኩላሊት ህክምና ማዕከል የ18 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ተፈራረመች።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና የኳታር ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ካሊፋ ቢን ያሲም አል ኩዋሪ  ተፈራርመውታል።

የኩላሊት ህክምና ማዕከሉ ባለ ስድስት ፎቅ ህንፃ የሚኖረው ሲሆን፥ በ77 አልጋዎች ለህሙማን አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ በሀገሪቱ የሚታየውን የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ችግር ያቃልላል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.