Fana: At a Speed of Life!

የታሪካዊው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል ሉቺያኖ ቫሳሎ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበሩት ሉቺያኖ ቫሳሎ ከዚህ ዓለም በሞት መለያተቸውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አስታወቀ።
ሉቺያኖ ቫሳሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ብቸኛው የሆነው እና ኢትዮጵያ አስተናግዳ አሸናፊ በሆነችበት 3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል ነበሩ።

 

በኤርትራ የተወለዱት ሉቺያኖ ለገጀረት ፣ ጂዲ አስመራ ፣ ጥጥ ማህበር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች በተጫዋችነት አሳልፈዋል።

 

ከዚህ ባለፈም ታሪካዊውው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአምበልነት በመምራት ስኬታማ የተጫዋችነት ጊዜን ያሳለፉ ታላቅ ተጫዋች ነበሩ።

 

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ የብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጎል አስቆጣሪ ሲሆኑ፥ ኢትዮጵያ ባሸነፈችበት 3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታም ጎል በማስቆጠር እና በአምበልነት ዋንጫውን አንስተዋል።

 

በአስመራ የተወለዱት ሉቺያኖ ከተጫዋችነት ባለፈ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጭር የአሰልጣኝነት ጊዜ ያሳለፉ ሲሆን ለረጅም ጊዜ በጣልያን ኑሯቸውን ማድረጋቸውን ሶከር ኢትዮጵያ በመረጃው አመላክቷል።

 

የሉቺያኖ ወንድም የነበሩትና በ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ጎል ያስቆጠሩት ኢታሎ ቫሳሎ ባለፈው አመት ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.