Fana: At a Speed of Life!

በአዳባ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከአዳባ ከተማ ወደ ላጆ ከተማ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ መኪና ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የተከሰተ መሆኑን የአዳባ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በደረሰው አደጋም የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ÷ 15 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በላጆ እና አዳባ ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በሻሸመኔ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መኪናው የመጫን ልኩ 28 ሰው ብቻ የነበረ ቢሆንም ከመጠን በላይ በመጫን 40 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ አደጋው መድረሱ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ በደረሰ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ዛሬ ከጠዋቱ 2፡00 ከሎጊያ ከተማ 15 ሰዎች አሳፍሮ ወደ አፍዴራ ይጓዝ የነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በኮሪ ወረዳ ልዩ ቦታው “ጉያህ” ተገልብጦ ሾፌሩን ጨምሮ አምስት ሰዎች ወዲያው ሕይወታቸው ማለፉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአደጋው በ10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት አጋጥሟቸው በዱብቲ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.