Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በቤኒሻንጉል ክልል ለቱሪዝም ቀን እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተደረገ ያለውን የቱሪዝም ቀን ዝግጅት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በአምባሳደሯ የተመራው  ልዑክ በዛሬው እለት በክልሉ የሚገኘውን  የሼህ ሆጀሌ አልሃሰን የችሎት አዳራሽን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የኢፌዴሪ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አቶ አብዱልሙኒየም አብዱልዋህድን ጨምሮ ፌዴራልና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

35ኛው የዓለም የቱሪዝም ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ከመስከረም 13 እስከ መስከረም 15 ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.