Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የትምህርት አስተዳደር ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል “ትምህርት ለሁሉም ሁሉም ለትምህርት” በሚል መሪ ቃል 25ኛው የትምህርት አስተዳደር ጉባዔ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የ2014 የትምህርት ዘመን አፈጻጸም እና የ2015 እቅድ እንደሚቀርብ ተጠቅሷል፡፡

የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ትምህርት ቤቶች ላይም የመስክ ምልከታ እንደሚደረግ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.