Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸውን የትብብር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ በተለያዩ መስኮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን የትብብርና የድጋፍ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ከዓለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ባለው የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋምና መከላከል ላይ እየተሰራ ባለው ስራ ዙሪያ መክረዋል፡፡

እንዲሁም ከብሄራዊ አካውንት መረጃ አያያዝና የተፈጥሮ ሃብትን በሀገራዊ ምርት እድገት ላይ ያለውን ድርሻ በተመለከተ ፤ መረጃ አያያዝን እና መረጃን በአግባቡ መጠቀምን በተመለከተ ውይይት መደረጉን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዓለም ባንክ የሚደርገውን ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስት በ 10 ዓመቱ የልማት እቅድ ዉስጥ ቅድሚያ እና ትኩረት በሰጣቸዉ መስኮች ላይ ማተኮር እንዳለበትም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

የዓለም ባንክ በተለያዩ መስኮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን የትብብርና የድጋፍ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ሃገሪቱ በጀመረቻቸዉና ቅድሚያ በምትሰጣቸዉ መስኮች ላይ ድጋፉን እንደሚያጠናክር አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.