Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል የፀጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የክልሉን ሰላምና ፀጥታን ለማጎልበት የተከናወኑ ተግባራት ገምግሟል።

በውይይቱም የክልሉን ሰላምና ፀጥታን ከማጠናከር አንፃር በተለይም ህገወጥ የጦር የመሳሪያ ዝውውር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና የነዳጅ ግብይትን ከመከላከል አንፃር የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል ረገድም የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትንና ህዝብን ባሳተፈ መልኩ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት÷ በክልሉ እየታየ የሚገኘውን አንፃራዊ ሰላም ከማስቀጠል አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የኢኮኖሚ አሻጥር በመፍጠር የኑሮ ውድነት እንዲባባስ የሚያደርጉ አካላት እና በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃርም የተጠናከረ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይም የሚከበሩ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህም በወረዳዎች እየተሰሩ የሚገኙ አበረታች ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ማለታቸውን ከሐረሪ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.