Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እውቅና እና ሽልማት ተሰጠ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2014 ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እውቅና እና ሽልማት ተሰጣቸው

 

በከተሞች እህትማማችነት ላይ አስተዋፅዖ ማበርከት አንዱ መስፈርት ሲሆን ከልማትና አገልግሎት አኳያ የተቀመጡ መስፈርቶችም በጦርነት ቀጠና ውስጥ የነበሩትን ታሳቢ በማድረግ የቀረቡ ናቸው።

 

ከተሞች ካላቸው መዋቅራዊ አደረጃጀት አኳያ እርስ በርስ እንዲወዳደሩ የተደረገ ሲሆን ከ32ቱ የክልሉ ከተሞች 18ቱ ተሳትፈዋል።

 

የአማራ ክልል የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ኢብራሂም ሙሃመድ እንዳሉት÷ እውቅናና ሽልማቱ የተሻለ የሰሩትን ለማበረታታትና ደካማ አፈፃፀም ያስመዘገቡትን በቀጣይ እንዲያስቡበት ለማድረግ ያለመ ነው።

 

የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች÷ የኮምፒዩተር ፣ የሞተር ብስክሌት ፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ፣የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

 

በልዩ ሽልማት ደግሞ ያለ ምንም በጀት ህብረተሰቡን በማስተባበር ከፍተኛ ስራ ላከናወነው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አንድ ሞተር ብስክሌትና አምስት ኮምፒውተሮች ሽልማት ተበርክቶለታል።

 

በሙሉጌታ ደሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.