Fana: At a Speed of Life!

“በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ያወጣው ረቂቅ ሪፖርት ባዶ የፖለቲካ ሪፖርት ነው” – የሱፍ ኢብራሂም

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ያወጣው ረቂቅ ሪፖርት ባዶ የፖለቲካ ሪፖርት መሆኑን አቶ የሱፍ ኢብራሂም ገለፁ።

የአብን ስራ አስፈፃሚ አባል እና የአለም አቀፍ ህጎች ባለሙያዉ አቶ የሱፍ ከፋና ቴሌቪዥን ስለ ኢትዮጵያ ፕሮግራም ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የወጣው ረቂቅ ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ላይ ጫና ለማሳደር የተዘጋጀ የፖለቲካ መሳሪያ ሰነድ ነው ብለዋል

አቶ የሱፍ፥ “እስካሁን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶች ወጥተዋል ነገር ግን በኢትዮጵያ ላይ እንደወጣው አይነት ባዶ የተዛባ እና ደካማ ሪፖርት ታይቶ አይታወቅም” ብለዋል።

ሪፖርቱ ከምርመራ ስነ ዘዴ ገለልተኝነት እና አለም አቀፍ የሰብዓዊ ምርመራ መመሪያ አንፃር ሲመዘን በይዘትም፤ በአሰራር ስነ ስርአትም፤ የተፋለሰ መሆኑም አቶ የሱፍ ተናግረዋል።

አያይዘውም ከመረጃ አሰባሰብ እስከ መረጃ ትንተና ከሙያዊነት በራቀ መልኩ የተሰናዳው ረቂቅ ሪፖርት፥ በብዙ መመዘኛ የመጥፎ እና ያልበሰለ ጥናት ውጤት ሆኖ ከመጠቀስ የዘለለ ሚና  አይኖረውም ነው ያሉት።

የሪፖርት ሰነዱ ከመግቢያው ጀምሮ የአሸባሪው ቡድን ህውሃትን ወንጀሎች በማሳነስ እና በመሸፋፈን መነሳቱን የተናገሩት የህግ ባለሙያው፥ ዋና ግቡም በተለያየ መልኩ አጣብቂኝ ወስጥ ያለውን አሸባሪ ቡድን መታደግ ነው ብለዋል።

ፖለቲከኛው እና የህግ ባለሙያው አቶ የሱፍ፥ ሰነዱ ሪፖርቱ ህውሃትን መታደግ ኢትዮጵያን ማዳከም የሚፈልጉ ሃገራት እና ተቋማት የሚፈልጉትም ድምዳሜ ካስቀመጠ በኋላ ለዚያ ድምዳሜ የሚሆን ግብአት ለማቅረብ የተሰናዳ የፖለቲካ ሰነድ ነው ሲሉም ተችተዋል።

በአጠቃላይ መንግስት ስራውን እንዳይሰራ፣ እንደማስፈራሪያ እና እንደ መሳሪያ የመጠቀም አካሄድ የታየበት መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሪፖርቱ የተፋለሰ ነው ያሉት ፖለቲከኛ እና የህግ ባለሙያው፥  ቢያንስ በሪፖርቱ ጦርነቱ የሽብር ቡድኑ ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት በማድረሱ መቀስቀሱን መጠቀስ እንደነበረበትም አንስተዋል፡፡

እንዲሁም ሽብርተኛው ህወሓት ለሰላሳ ዓመታት የፈፀመውን ሰቆቃ  በሪፖርቱ መግቢያ ሊጠቀስ ይገባ እንደነበር አስገንዝበዋል።

በፌቨን ቢሻው እና የሻምበል ምኅረት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.